የእምነት አንቀጽ

1, ሁሉን በሚችል ፍጹም በሆነ ሰማይንና ምድርን እንዲሁም በውስጧ ያሉትን ሁሉ በፈጠረና በሚገዛ ለዘለአለምም በአንድነትና በሶስትነት በሚኖር በእግዚአብሔር አብ ፥ በእግዚአብሔር ወልድና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እናምናለን። (ዘፍ:1 ዮሐ17፥3 ራዕ 4፥11)
2, ፍጹም እግዚአብሔር ፍጹም ሰው በሆነ ከመንፈስ ቅዱስ ተጸንሶ ከድንግል ማርያም በተወለደ ለሰው ልጆች ሁሉ ኃጢአት ሲል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በሞተ ፥ በተቀበረ ፥ ወደ ሲኦል በወረደ ፣ በሶስተኛው ቀን በሥጋ ከሞት በተነሳ ፣ ወደ ሰማይ ባረገ ፥ አሁን ሊቀካህናችንና ጠበቃችን ሆኖ በአባቱ ቀኝ ባለ ፥ ተመልሶ በክብር በሚመጣ በአብ ልጅ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን። (ማቴ 1፥8 ዮሐ 1፥1 ዮሐ 3፥16 ዮሐ 14:1-2 ዕብ :3-8 ዕብ 9፥ 24 1ኛ ቆሮ 15: 3-4)
3, ክርስቶስን በሚያከብር ሰዎችን ስለ ኃጢአት በመውቀስ ዳግም እንዲወለዱ በሚያደርግ በአማኞች ውስጥ በመኖር በሚመራና በሚያስተምር ለተቀደሰም ኑሮና አገልግሎት በኃይሉ በሚያስታጥቅ ፥ በስጦታዎቹም በሚሞላ የእውነት መንፈስ በሆነው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እናምናለን። (ዮሐ 14፥26-27 ዮሐ 15፥26 ዮሐ 16: 7-14 1ኛ ቆሮ 12፥2-11)
4, መጽሐፍ ቅዱስ 39 የብሉይ ኪዳንና 27 የአዲስ ኪዳን ፤ በጥቅሉ 66 መጻሕፍት ሆኖ ሰዎች በእግዚአብሔር መንፈስ ተነድተው የጻፉት ፥ እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጆች ደኅንነት የገለጸበት ሊጨመርበት ወይንም ሊቀነስበት የማይገባ ብቸኛ በጽሑፍ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነና ለአማኞች እምነትና ኑሮ አዛዥ ፥ መሪና ባለሙሉ ሥልጣን መሆኑን እናምናለን። (2ኛ ጢሞ 3:16-17 2ኛ ጴጥ 1:19-21 ኢያ 1፥8)
5, ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥሮ በሀጢአት የወደቀና በመንፈስ የሞተ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን የመስቀል ሥራ አምኖ በመቀበል ዳግም ልደትና ደኅንነትን እንዲሁም ሕያው የሆነ መንፈሳዊ ሕይወትን እንደሚያገኝ እናምናለን። (ዘፍ 1፥26 ኤፌሶን 2፡1-2 ቲቶ 3:3-7)
6, ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔር የተፈጠሩ በጎ የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲፈጽሙና በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ሰውን በተለይም አማኝን ከእግዚአብሔር ተልከው እንደሚረዱ እናምናለን። (ዕብ 1፥14)
7, ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ አምጾና ሌሎቹንም መላእክት አሳምጾ ከእግዚአብሔር ክብር ፊት የተጣለ የሀሰት ሁሉ አባት ፥ የኃጢአት ሁሉ ምንጭ እንደሆነና አብረውት የወደቁት ርኩሳን መናፍስትም የእግዚአብሔርና የሰው ልጆች ጠላቶች እንደሆኑ እናምናለን።(ራዕ 12፥7:9)
8, ለሚያምኑ ሁሉ የክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ የጽድቅና የደኅንነት መንገድ መሆኑን ፥ ይህንን በእምነት የተቀበሉ ብቻ ከመንፈስ ቅዱስ ተወልደው የእግዚአብሔር ልጆች እንደሚሆኑና የዘላለምን ሕይወት እንደሚወርሱ እናምናለን። (ሐዋ 4፥12 ቆላ 1፥20 ሮሜ 6:5-6 ቲቶ 3:5-7)
9, የአማኝ የውሀ ጥምቀትና የጌታ እራት የተቀደሱ ስርዓቶችና መታሰቢያዎች ሲሆኑ ቤተ ክርስቲያን በእነዚህ ሥርአቶች መካፈልና ሥርአቶቹን መጠበቅ እንዳለባት ፥ ነገር ግን እነዚህ ሥርአቶች የደህንነት መቀበያ መንገዶች እንዳልሆኑ እናምናለን። (ማቴ 28፥10 ሐዋ 8፥36-39 ሐዋ፥16፥31-33 1ኛ ቆሮ 11፥23)
10, መሠረቷና ራሷ ክርስቶስ በሆነ በጌታ ኢየሱስ ሥራ አምነው ደኅንነትን የተቀበሉ እና የተጠመቁ ሁሉ በታቀፉባት በአንዲት ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። የዚህችም የማትታየዋ ቤተ ክርስቲያን አባላት የሆኑት ብቻ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባላት መሆን እንደሚገባቸውና እንዳለባቸው እናምናለን። (ኤፌ 1፥22 4፥4 ቆላ 1፥18 ሐዋ 2 )
11, ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ ስለሆነ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ራስነት ራሷን የመምራትና የማስተዳደር መብትና ሥልጣን እንዳላት እናምናለን፡፡ (ኤፌ 1፥22 ቆላ 1፥18)
12, የሞቱት ሁሉ በሥጋ ትንሳኤ ከሞት እንደሚነሱና አማኞች ከጌታ ጋር ወደ ዘላለም በረከትና ደስታ፥ የማያምኑት ደግሞ ወደ ዘላለም ፍርድና ቅጣት እንደሚሄዱ እናምናለን።(ራዕ 20፥6 ዮሐ 5፥28-29 1ኛ ቆሮ 15፥20-23 ፥ 50-58)
13, ጋብቻ ቅዱስ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ብቻ እንደሆነ እናምናለን::
14, ጌታ ኢየሱስ ዳግም እንደሚመጣና ምድርን ለሺህ ዓመት እንደሚገዛ ፥ የፊተኛውን ትንሳኤ ያገኙ ቅዱሳንም ከእርሱ ጋር በመሆን በሺህ ዓመቱ አገዛዝ እንደሚነግሱ እናምናለን። (ራዕ 20፥ 1-6)
15, የሺህ አመት ሲፈጸም የቀደሙት ሰማይና ምድር በእሳት ተቃጥለው ያልፋሉ። በነጩ ዙፋን ሥር ግን ቅዱሳን በአዲስ ሰማይና ምድር (አዲሲቷ ኢየሩሳሌም) ለዘለአለም ወደ እረፍቱ ሲገቡ በሕይወት መዝገብ ስሞቻቸው ተጽፎ ያልተገኙት ደግሞ ለሰይጣንና ለመልአክቱ ወደ ተዘጋጀው እሳት ለዘላለም እንደሚጣሉ እናምናለን።

Our Faith

1. We believe in one God, Greater of all things, holy, infinitely perfect, and eternally existing in a loving unity of three equally divine Persons: the Father, the Son and the Holy Spirit. (Gene.1 , John 17:3, Rev. 4:11).
2. We believe that Jesus Christ is fully God and fully man, was conceived through the Holy Spirit and born of the Virgin Mary. He was crucified on the cross for our sins, arose bodily from the dead, ascended into heaven and sits at the right hand of God the Father as our High Priest and advocate, will return to judge the living and the dead. (Matthew 1፥8 John 1፥1 John3፥16 John 14:1-2 Hebrews :3-8 Hebrews 9፥ 24 1Cor. 15: 3-4)
3. We believe that the Holy Spirit glorifies the Lord Jesus Christ. He convicts the world of its guilt. He regenerates sinners, and in Him they are baptised into union which Christ and adopted as heirs in the family of God. He also indwells, illuminates, guides, equips and empowers believers for Christ-like living and service. (John 14:26-27, John 15:26, John 16:7-14, 1sT Cor.12:2-11).
4. We believe that the Bible consists 66 books of the Old and New Testaments. God’s authentic and inspired written communication for all people. Full of truth, with no mistakes in it. Shall not add or take away from it. (2Tim. 3:16-17 2Peter 1:19-21 Joshua1፥8)
5. We believe that human beings are sinners by nature and by choice, alienated from God, and under His wrath. Only through God’s saving work in Jesus Christ can we be rescued, reconciled and renewed. (Genesis1፥26 Romans1፥12 Titus 3:3-7)
6. We believe that angels are created by God as God’s messengers to mankind and defend, assist and protect God’s people. They are all ministering spirits, sent out to do service for the sake of those who will inherit salvation. (Hebrews 1፥14)
7. We believe that God threw Satan to the earth because he was rebellious against God and wanted to make himself the Most High and desired to be God. (Revelation 12፥7:9)
8. We believe that to all who believe Christ’s death and resurrection is the way to salvation, born from the spirit, become God’s children and will inherit everlasting life. (Acts 4፥12 Col. 1፥20 Romans 6:5-6 Titus 3:5-7)
9. We believe that water baptism and Lord’s Supper for believers are holy practices of the church that was instituted by the Lord Jesus himself, as testimonies to faith in Him. (Mat. 28፥10 Acts 8፥36-39 Acts፥16፥31-33 1Cor 11፥23)
10. We believe that the church is the body of Jesus Christ that composes all who have been justified by God’s grace through faith in Christ where Christ is the head. Those members of the invisible church who have been redeemed and are truly Christian have to be member of local churches. (Eph. 1፥22 4፥4 Col. 1፥18 Acts 2)
11. We believe that as Christ is the head of the body, local churches have the authority to govern themselves. (Eph. 1፥22 Col.1፥18)
12. We believe in the physical resurrection of all human beings. The unbelievers shall cast into the lake of fire to suffer everlasting punishment, believers to eternal blessedness and joy with the Lord. (Rev. 20፥6 John 5፥28-29 1Cor 15: 20-23 ፥ 50-58)
13. We believe that marriage is holy and it is a covenant between a man and a woman.
14. We believe that the Lord Jesus Christ will return to earth, the resurrected Saints reign with Christ for a thousand years. (Revelation 20፥ 1-6)
15. We believe that when a thousand years come to an end heavens and earth will be burned up in God’s judgement, replaced by new heavens and a new earth (the new Jerusalem) in which righteousness dwells for everlasting peace but those whose names are not found in the book of life will be cast into the eternal fire which is prepared for the devil and his angles